ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Joined June 2020
#FactCheck ኢትዮጵያ በ2026 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ‘ከፍተኛ የተባለውን’ የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ IMF አስታውቋል? ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እኤአ የ2026 እና 2027 ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በርካታ ሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ። በዚህ ዙርያ ያደረግነውን ማጣራት ያንብቡ ⤵️ ethiopiacheck.org/%e1%8a%a2%…
1
727
#FactCheck ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከቦታቸው እንደተነሱ የሚጠቅስና በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ የሚገኘው ደብዳቤ ፌዝ አዘል እና ሀሰተኛ ነው በኢንስቲትዩት ኦፍ ኮመንዌልዝ ተማራማሪ የሆኑትና በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት ማርቲን ፕላውት ደብዳቤውን ካጋሩ በኋላ “ሀሰተኛ እንደሆነ ተነግሮኛል፣ አጥፍቸዋለሁ፣ ይቅርታ” በማለት ከገጻቸው አንስተውታል ሙሉ መረጃውን ያንብቡ: ethiopiacheck.org/%e1%8d%8a%…
3
6
1
18
4,488
#FactCheck እነዚህ ምስሎች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ያረጉትን ንግግር እና የተመድ ዋና ፀሐፊ ምላሽ አያሳይም /ኢትዮጵያ ቼክ/ -- ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ እየተካሄደ ባለው የ81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሰናባቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር አደረጉ የተባለው ቃላት ምልልስ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ ቪዲዮ በዚህ ሳምንት በርካታ ተከታዮች ባላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እየተጋራ እና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገደ ይገኛል። ይህን ቪዲዮ መረጃ ካጋሩ መካከል Umut Cagri Sari የተባለ ኤክስ ላይ ከ10 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ ይገኛል: በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ወደ 91 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 14 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። በተመሳሳይ 1991 የተባለ ከ 1,700 በላይ ተከታዮች ያሉት የኤክስ ገፅ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 198 የሚሆኑ የኤክስ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 32 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። በተጨማሪም በርካታ የኤርትራ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ የሚጠቁሙ አካውንቶች መልዕክቱን በስፋት አሰራጭተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በቪዲዮ ምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከሰሞኑ የተደረገ ምልልስ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት በመፈለግ ባደረግነው ማጣራት ቪዲዮው ፕሬዝደንት ታዬ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእከተኛ በነበሩበት ጊዜ መስከረም 26 2014 የተደረገ የቃላት ምልልስ መሆኑን አረጋግጧል: youtu.be/Sy3zq422Gj4?si=adIW… በዚህ ሰሞን ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ ኒው ዮርክ ያደረጉትን ንግግር ቪዲዮ በተለያዩ ተቋማት ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል: youtu.be/d0ekOP-ts_Y?si=wDwm… በዚህም መሰረት ስለዚህ እነዚህ ቪዲዮች ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል። በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
2
567
#FactCheck አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የወደቀን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮን ያሳያል የተባል ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ እንደሚገኝ ተመልክተናል። በምስሉ ‘የኢትዮጵያ አየር ኃይል ETHIOPIAN AIR FORCE’ የሚል ጽሁፍ ያለበት ድሮን ኮረብታማ አካባቢ ወድቆ ይታያል። ከበስተኋላው ደግሞ ሚሊተሪ እና ሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች እየጨሰ ወደሚገኘው ድሮን ሲራመዱ ይታያሉ። ይህን ምስል ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Zelalem Hailu (One Amhara fano)’ የሚል ስም እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ይገኝበታል። ገጹ “አንድ በሉ!….” ከሚል ጽሁፍ ጋር ምስሉን ያጋራ ሲሆን ልጥፉ በርከት ያሉ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል። የጉግል ምርት የሆነውንና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ምስሎች፤ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለመለየት የሚረዳው ሲንት አይዲ ዲቴክተርን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ በከፍተኛ እርግጠኛነት (very high confidence) በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ተመልክተናል። በሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተፈብርከው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየታዩ ሲሆን በርካቶችን ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሲዳርጉም ይስተዋላል። በመሆኑም በማህመራዊ ትስስር ገጾች የሚጋሩ አጠራጣሪ የሆኑና ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠ ምስሎችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
1
6
1,004
እንኳን አደረሳችሁ! መልካም አዲስ ዓመት!
3
455
#FactCheck እነዚህ ምስሎች ሰሞኑን በምስራቅ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂዎች የወደመ የአርሶ አደር ቡና ማሳን አያሳዩም /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በመንግስት ጸጥታ አካላት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መከሰቱ ሲዘገብ ሰንብቷል፣ በግጭቱ ምክንያትም በርካታ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸው እንዲሁ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዞኑ በፋኖ ታጣቂዎች የወደመን የአርሶ አደር ቡና ማሳ ያሳያሉ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። እነዚህ ከትላንት ረቡዕ ነሀሴ 27፣ 2018 ጀምሮ እየተዘዋወሩ የሚገኙ ምስሎች በርካታ ተከታዮች ባላቸው የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች ጭምር እየተጋሩ አና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገዱ ይገኛሉ። ይህን መረጃ ካጋሩ መካከል ‘Alex Taye’ የሚል ስምና ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት አካውንት አንዱ ሲሆን “ይህ የፋኖ ጽንፈኞች ያወደሙት የወለጋ አርሶ አደር ቡና ነው” ከሚል ፍሁፍ ጋር ምስሎቹን አጋርቷል። በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ከ300 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን ከ700 በላይ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ከሰሞኑ የተነሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት በመፈለግ (Reverese image search) ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከአመት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው የነበሩ እንደሆኑ ተመልክተናል። በወቅቱ ምስሎቹን ያጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችም ምስሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ውስጥ የተነሱ እንደሆኑ በመጥቀስ ነበር ምስሎቹን ያጋሩት፡ facebook.com/share/p/18N8Jj6… የቆዩና ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
4
45
7
95
9,763
#FactCheck የሳውዲው 'Al Riyadh' ጋዜጣ ያወጣው ነው በሚል ተቀናብሮ የተሰራጨው ፅሁፍ እና ምስል ሀሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- የሳውዲው Al Riyadh ጋዜጣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን እግር ሲስሙ ያሳያል የሚል ዜና ሰርቷል በሚል አንድ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ምስሉንና አርእስተ ዜናውን ካጋሩት መሀል ፋሲል የኔአለም 'Fasil Yenealem' የተባለ በፌስቡክ ላይ ከ269 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ ይገኛል። በተጨማሪም ኤክስ ላይ ወደ 23ሺህ የሚጠጋ ተከታዮች ያሉት @Joe የሚባል የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ መረጃውን አጋርቷል። ይሁንና ኢትዮጽያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ምስሉም፣ ዜናውም Al Riyadh ጋዜጣ ላይ እንዳልወጣ አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቼክ Google Lens የተባለ የድህረ ገፅ መረጃ ማጣሪያ በመጠቀም ባረገው ማጣረት የ Al Riyadh አርእስተ ዜና ርእስ የሚጠቀማቸው የአረብኛ ቃላቶች ልዩ ደማቅ ጥቁር የአረብኛ ፅሁፍ ጥበብ እንደሚጠቀም እና አረንጓዴ ቀለም ያለው የቴምር ዛፍ መለያው እንደሆነ አረጋግጧል: alriyadh.com/ በተጨማሪም Al Riyadh ጋዜጣ አመተ ምህረቱን የሚያስገባው ከአርእስቱ በታች በግልፅ በአውሮፓውያን አመተ ምህረት አቆጣጠር ተጠቅሞ በአግድም መልክ እንደሚያስቀምጥ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና የኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድን ያሳያል የተባለው ምስል የAl Riyadh ጋዜጣ መለያ የሆነውን አረንጓዴ የቴምር ዛፍ ሳይሆን የተባበሩት አረብ ኤምሬቴስ መለያ የሆነውን የወርቅ ቀለም ያለው መለያ ምስል በጉልህ ይታያል። በተጨማሪም የAl Riyadh ጋዜጣ ሌላ መለያው የሆነውን አመተ ምህረት አገባብ፣ ፊደልና የአውሮፓውያን አመት አቆጣጠር አያሳይም። የሰው-ሰራሽ አስተውሎት በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ወጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
1
3
3
907
#FactCheck ሰሞኑን በሻምቡ ከተማ ‘ለመንግስት እጃቸውን የሰጡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን ያሳያሉ’ በሚል እየተሰራጩ ያሉ ምስሎች የቆዩ ናቸው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ከሰሞኑ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ለመንግስት እጃቸውን የሰጡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን ያሳያሉ በሚል በርከት ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጩ ይገኛሉ። ይህን መረጃ በሰበር ዜና መልኩ ካሰራጩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Ethiopian Green Legacy’ የሚል ስም እና ከ27 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ ይገኝበታል። ገጹ “የጠላት ካምፕ መፍረሱን ቀጥሏል። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ የኦነግ ሼኔ (WBO) አባላት በጃል ያዴሳ የሚመሩት ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ በሰላማዊ መንገድ ለወታደራዊ መንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል” የሚል ጽሁፍም ከምስሎቹ ጋር አጋርቷል። በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች በርከት ያሉ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶችም ይህን መረጃ ያጋሩ ሲሆን አንዳንዶቹ እጃቸውን የሰጡ የታጣቂ ቡድኑ አባላት ቁጥር 200 እንደሚሆኑ ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን የተነሱ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። በዚሁ መሰረት ምስሎቹ የዛሬ ዓመት አከባቢ (እኤአ መስከረም 29፣ 2025) በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተጋሩ ሲሆኑ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርደጃ ጃርቴ ወረዳ “በሰላም የገቡ” የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላትን እንደሚያሳዩ ተዘግቦ ነበር። በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ዘገባ ከሰሩ መገናኛ ብዙሃን መካከል EBC አንዱ ሲሆን 73 የታጣቂ ቡድኑ አባላት “እጅ ሰጥተዋል” ሲል ዘግቦ ነበር፡ facebook.com/share/1Hiz34qqM… የቆዩና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
3
2
604
#FactCheck አልጀዚራ ስለ ምክክር ጠቅላላ ጉባኤ ሰራው በሚል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ተቀናብሮ የተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ /ኢትዮጵያ ቼክ/- አልጀዚራ የዜና ወኪል ስለ ኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ ሰራው የተባለ ሀሰተኛ ዘገባ በጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። ይህ የተሰራጨው የጽሁፍ እና ቪዲዮ መረጃ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያከናወነችው የጠቅላላ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ የውስጥ አለመግባባቶችን በጠመንጃ ግጭት ሳይሆን በውስጣዊ ውይይት ማስተናገድ እንደምትችል ያሳያል በሚል ተዘግቧል ይላል። ይህ የተሰራጨው የጽሁፍና የቪዲዮ መረጃ የምክክር ጠቅላላው ጉባኤው ውጤቶች ኢትዮጵያን ለሰላምና አካታች ልማት አቅጣጫ ሊመራት ይችላል ይላል። ይህን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በስፋት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ''Hermen Gashaw'' የተባለ ወደ 21 ሺህ ተከታዮች ያሉበት ገፅ ይገኛል። በገጹ የተጋራዉን ይኸንን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ ወደ 208 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ለሌሎች ያጋሩት ሲሆን 51 የሚሆኑ አስተያየቶች ሰጥተውበታል። ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ቪዲዮው እውነተኛ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነዉን ‘ሲንዝ አይዲ ዲቴክተር’ (SynthID Detector) የተባለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በመጠቀም በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተሰራጨው ፅሁፍ ትክክለኛ የዜና አቅራቢም፣ ዘገባም እንደማያሳይ ደርሶበታል። በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት በቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ምስልም ሆነ የሚሰማው ድምጽ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተቀነባበረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። በቪዲዮው ላይ የ'ዜና አቅራቢው' ቪዲዮ የሚታየው የከንፈር እንቅስቃሴ፣ የፊት ገጽታ እና የድምጽ ቅንብር አንድን ትክክለኛ ሰው አስመስሎ በኮምፒውተር ፕሮግራም የተሰራ እንጂ በገሃዱ ዓለም የተፈጠረን ዘገባ ክስተትን የሚያንጸባርቅ አይደለም። በተጨማሪ ቪዲዮው Hermen Gashaw በተባለ የፌስቡክ ገፅ የተጫነ እንጂ በተረጋገጡ አልጀዚራ እንግሊዘኛ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ የሌለ መሆኑን አረጋግጠናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ መሰል የዲፕፌክ (Deepfake) ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም እየተበራከቱ እና በርካታ ሰዎችን ለተሳሳተ መረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ። አሳሳች መረጃ አሰራጪ አካላት እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም እውነተኛ የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ። ይህ አይነቱ ቴክኖሎጂ የፖለቲካ ውዥንብር ለመፍጠር፣ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማራመድ፣ እና የሰዎችን ስነልቦና ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚሰራጭ አደገኛ የሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) መሳሪያ ሆኗል። በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ በማቅረብ ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃን አምኖ እንዲቀበል ማድረግ የተለመደ የማጭበርበር ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል። ሰዎች እውነተኛ ቪዲዮ እየተመለከቱ እንደሆነ በማሰብ እንዲታለሉ እና የተዛባ መረጃን ለሌሎች በማጋራት በማህበረሰቡ ውስጥ አለመተማመንን መፍጠር የዚህ አይነቱ ተግባር ዋና አላማ ነው። ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን እያደገ የመጣውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አደጋ በሚገባ ተገንዝበው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን። ማንኛውም አጠራጣሪ እና ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች ወይም ግለሰቦች የሚጋሩ የምስል እና የቪዲዮ መረጃዎችን ልክ እንዳዩት ከማመናችን እና መልሰን ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት ማድረግ አለብን።
1
3
5
877
ቪዲዮዎች ያልተለመደ የዓይን ብልጭታ፣ ከድምጽ ጋር የማይሄድ የከንፈር እንቅስቃሴ ወይም ኢተፈጥሮአዊ የሆነ የቆዳ ገጽታ ካላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ቼክ!
1
155
#FakeAccountAlert በመአረግ አማረ ስም ስለተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ የወጣ ማሳሰቢያ /ኢትዮጵያ ቼክ- በማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎው በሚታወቀው በመአረግ አማረ ስም እና ምስል የተከፈተ አንድ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ መረጃዎችን እያጋራ መሆኑን ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራት ከ15 ሺህ በላይ ተከታታዮች ያሉት ገፁ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። መአረግ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፁ ከ152 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት ብቻ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ያረጋገጠ ሲሆን ገፁንም በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡ facebook.com/share/1D91gjpkC… በታዋቂ ግለሰቦች እና ተቋማት ስም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ። እነዚህ አካውንቶች የሰዎችን አሳሳች መረጃ የማሰራጨት፣ የማጭበርበር እና የስም የማጥፋት ድርጊቶችን በቀላሉ ለመፈፀም ስለሚጠቀሙባቸው ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል። ብዙ ጊዜ እነዚህ ገፆች የህዝብን ትኩረት እና እምነት ለማግኘት የታዋቂ ሰዎችን ማንነት በመስረቅ ያልተረጋገጡ የፖለቲካ እና የብሄር ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን ያሰራጫሉ። በተጨማሪም ከባድ የፋይናንስ ማጭበርበሮችን በማካሄድ የውሸት የእርዳታ ጥሪዎችን በማቅረብ እና ሰዎችን የገንዘብ ወጥመድ ውስጥ በመክተት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደርሳሉ። ይህ ድርጊት የእውነተኛ አካውንት ባለቤቶችን መልካም ስምና ዝና ከማበላሸቱ ባሻገር ተከታዮች እውነተኛውን ከሀሰተኛው ለይተው ለማወቅ እንዲቸገሩ በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች ላይ ያለውን እምነት ያጠፋል። ስለሆነም የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እንዲሁም ምስል በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ ገፆች ለእንደነዚህ አይነት አሳሳች አደጋዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ሁልጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። ተጠቃሚዎች ማንኛውንም መረጃ ከማመናቸው እና ከማሰራጨታቸው በፊት የገፁን የሰማያዊ ምልክት (Verification Badge)፣ የተከፈተበትን ጊዜ፣ የፖስቶች ይዘት እና የተከታዮች ብዛት በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው። በተጨማሪም ሀሰተኛ እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገፆችን እና ቻናሎችን ለመለየት የሚረዱ ጠቋሚ ምልክቶችን ለመመልከት በኢትዮጵያ ቼክ የተዘጋጀውን ይህን አጭር ቪዲዮ መመልከት ትችላላችሁ፡ t.me/ethiopiacheck/1344 ኢትዮጵያ ቼክ!
541
#FactCheck በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ወደቀ ስለተባለው ጄት እየተሰራጩ ያሉ ትክክለኛ እና አሳሳች መረጃዎች /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ጎራ ለመን ቀበሌ ወደቀ ስለተባለ የጦር ጄት የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። የጄቱ ስብርባሪ አካል ብቻውን እንዲሁም የታጠቁ ሰዎች በስብርባሪው ላይ ቆመው የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎችም እየተጋሩ ይገኛሉ። አንዳንዶች የጦር ጄቱ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ታጣቂዎች ተመቶ መውደቁን በመጥቀስ ምስሎቹን ያጋሩ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ምስሎቹ እና ቪዲዮዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ እንደሆኑ የጻፉም አሉ። በተጨማሪም ምስሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጄትን እንደማያሳይ በመጥቀስ መረጃው ሀሰተኛ እንደሆነ የጻፉም አሉ። ከነዚህ መካከልም ‘Demeke Negassa Kube’ የሚል ስም እና ከ500 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። ገጹ “የወያኔ ቋሚ ተላላኪዎች እያሰራጩ ያለው ዜና በፍጹም ውሸት ነው ።ጀግናው አየር ኃይላችን እንደዚህ ጨጨባ (ስብርባሪ) ጄት የለውም።ይህንን ስብርባሪ ለራሣችሁ አውሉት።በመንደር ሽፍታ ቀርቶ በሌላም በቀላሉ የሚመታ ጄት የለውም” ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ስለሚገኙ ምስሎች እና ቪዲዮ ጽፏል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ እና ቪዲዮ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹም ሆነ ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲሁም በቅንብር የተሰሩ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። በተጨማሪም ምስሎቹ እና ቪዲዮ ከዚህ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው እንደማያውቁም ተመልክቷል። የጦር ጄቱም ኤሮ L-39 አልባትሮስ (Aero L-39 Albatros) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክ ስሪት ነው። ይህ ጄት በስፋት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ሲሆን ለአየር ላይ ውጊያ፤ የመሬት ላይ ኢላማዎችን ለማጥቃት እንዲሁም ለስለላ አገልግሎትም መዋል ይችላል። የኢትዮጵያ አየር ኃይልም ይህን ጄት ለስልጠና እንደሚጠቀም ከዚህ በፊት የተጠቀሰ ሲሆን ጄቱ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ በተከበረው የአየር ኃይል 90ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ትርዒት ካሳዩ ጄቶች መካከል አንዱ ነበር። በእለቱም የተወሰኑ የአየር ኃይሉ L-39 አልባትሮስ ጄቶች ትርዒት ያሳዩ ሲሆን የጄቶቹ ትርዒት EBC በእለቱ ባሰራጨው ቀጥታ ስርጭት ቪዲዮ 1፡03፡00 ጀምሮ ይታያል፡ youtube.com/live/Ib4t9boBZxg… በዚህ የEBC ቪዲዮ ውስጥ 5፡30 ደቂቃ ላይ ደግሞ ጄቶቹ በረድፍ ቆመው ይታያሉ፡ youtu.be/969VaWBL9EY?si=cJFb… በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ የተከሰከሰውን ጄት ስብርባሪና በክብረ በዓሉ ላይ ትርዒት ያሳዩ L-39 አልባትሮስ ጄቶችን በማነጻጸርም ተመልክቷል። በዚሁ መሰረት የተከሰከሰው እና በትርዒቱ ላይ የተሳተፉት ጄቶች ተመሳሳይ የቀለም ስብጥር እንዳላቸው አረጋግጧል። ከነዚህ መካከልም ጄቶቹ ሆድ ስር የሚገኘው ሰማያዊ ቀለም፤ ክንፎቹ ጫፍ ላይ ያሉት ቀይ እና ቢጫ ቀለማት እንዲሁም የጄቶቹ ጅራት ጫፍ ላይ የሚገኘው ቢጫ ቀለም ቅብ ይገኙበታል። ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች እንዲሁም በጄቱ ስብርባሪ ምስል ላይ የሚታየውና ጄቱ እንደወደቀ የተገለጸበት ስፍራ መሬት አቀማመጥ መመሳሰል ጄቱ ከጥርጣሬ በላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው። ይሁን እንጂ ጄቱ ተመቶ ወይስ በቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የወደቀው የሚለው ጥያቄ በማስረጃ ያልተመለሰ ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ስለ ጉዳዩ በግልጽ ያሉት ነገር የለም። ኢትዮጵያ ቼክ
1
4
10
1,830
#FactCheck በሸረሪና የተማረኩ 'የህወሓት ኃይሎች እና ጦር መሳሪያዎች' በሚል እየተሰራጩ የሚገኙት ምስሎች የቆዩ ናቸው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ሰሞኑን በፌደራል ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሸረሪና አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። ይህን ግጭት መነሻ በማድረግም በፌደራል ሠራዊት የተማረኩ ‘የትግራይ ኃይሎች’ አባላት እና ጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ በሚል በርከት ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። እነዚህን ምስሎች ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከልም ‘አውደ ሀገር’ የሚል ስም እና ከ107 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። በዚህ ገጽ የተጋራውን የምስል እና ጽሁፍ መረጃ 19 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ሲያጋሩት በርከት ያሉ አስተያየቶችም ተሰጥቶበታል። በተጨማሪም ‘Mimi Jarso’ የሚል ስም እና ከ170 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ተመሳሳይ መረጃን አጋርቷል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ሸረሪና አከባቢ በተከሰተው ግጭት የተማረኩ የትግራይ ኃይሎች አባላትን እና ጦር መሳሪያዎችን እንደማያሳዩ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት መፈለጊያ ድረ-ገጾችን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከወራት በፊት በአማራ ክልል ውስጥ የተነሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል። በዚሁ መሰረት ምስሎቹ እኤአ ታህሳስ 15፣ 2025 “በምስራቅ ደምቢያ እና በቆላድባ ከተማ አካባቢ ታጥቀዉ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለዉ ገቡ” በሚል ርዕስ በአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ የተጋሩ ናቸው፡ facebook.com/share/14hssp5ab… ስለዚህም ምስሎቹ ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል። በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
1
3
1
6
1,598
#FactCheck የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አማካሪ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ አቋም ወስደዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የአረብ አገራት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አገራቸው በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ የጠነከረ እርምጃ ትወስዳለች ብለው ተናግረዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ መሠረት የሌለውና ሐሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል። ከ193 ሺህ በላይ ተከተዮች ያሉት «ጌትነት አልማው ጥሩነህ» የተባለው የፌስቡክ ገፅ ይህ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊ «ፀረ-ኢትዮጵያ አደረጃጀቶች ላይ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግረዋል» በሚል የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል። ይህ የፌስቡክ ገፅ ያሰራጨው መረጃ አሳሳች መሆኑ ሳይታወቅ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መልሶ እንዲሰራጭ እና የህዝብን ትኩረት እንዲስብ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ጥልቅ ማጣራት እንደሚያሳየው ማሳድ ቡሎስ በይፋዊ የኤክስ (X) ገፃቸው ላይ ባጋሩት መግለጫ አሜሪካ የተባለውን ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚል ንግግር አላደረጉም። ማሳድ ቡሎስ በሰጡት ቀጥተኛ ማብራሪያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያተኮረው የአሜሪካ ዲፕሎማሲ «ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረትን ለማጠናከር እየሞከረ ነው» ተብለው በየቦታው የቀረቡት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ ውሸት አሳሳችና ህዝብን የሚያሳስቱ መሆናቸውን በግልጽ አስረድተዋል። በተጨማሪም አሜሪካ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድና የሰፊው ቀይ ባሕር ቀጣና አገሮች ጋር በጋራ የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በቅርበትና በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። የአሜሪካ ዲፕሎማሲ ዋነኛ አላማ ተፎካካሪ ጎራዎችን መፍጠር ወይም የቀጣናውን ቅራኔዎች ማጥበቅ ሳይሆን ግጭቶችን በማስቀረት ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አብራርተዋል። በሌላ በኩል መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው «አፍሪካ ሪፖርት» (The Africa Report) የተባለው የዜና ምንጭ በቅርቡ ባወጣው የትንታኔ ዘገባ የአሜሪካ ዲፕሎማሲ በግብፅ-ሶማሊያ-ኤርትራ ምህዋር በኩል እና በኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ-እስራኤል ምህዋር በኩል ባለው አህጉራዊ ፖለቲካዊ ውጥረት መካከል ሊወጠር እንደሚችል አመላክቷል። ይህ የትንታኔ ዘገባ የቀጣናውን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያስረዳ እንጂ ማሳድ ቡሎስ እርምጃ እወስዳለሁ ብለው የተናገሩትን የሚያረጋግጥ አይደለም። በፖለቲከኞች፣ በዲፕሎማቶች እና በታዋቂ ሰዎች ስም ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩ አስመስሎ ማሰራጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረግ የተለመደ የሐሰተኛ መረጃ (Disinformation) ስልት ነው። ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች በሚያነቡበት ጊዜ፣ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገፅ ታማኝነትና ትክክለኛነት አስቀድመው እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ ይመከራል። ኢትዮጵያ ቼክ!
1
506
#FactCheck በአሜሪካ የአማራ ማህበር ስም የተሰራጨው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታወቀ /ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሰሞኑ በስፋት ሲሰራጭ የነበረውንና በአሜሪካ አማራ ማህበርን (AAA) የደብዳቤ ቅርፅ እና አርማ የያዘውን መግለጫ አስመልክቶ ማህበሩ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አጋርቷል። በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚል ቀን የተጻፈበትና የአሜሪካ አማራ ማህበርን ህጋዊ አርማ የያዘ የአቋም መግለጫ በሰፊው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። ይህ በስፋት የተሰራጨው መግለጫ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል አቅጣጫና የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ሀሳቦችን ያካተተ ነው ተብሎ ነበር። ነገር ግን መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ የአሜሪካ አማራ ማህበር በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ይፋዊ ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ማህበሩ በላከው መግለጫ መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ በማህበሩ ያልተዘጋጀና ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ጠቁሟል። ድርጅቱ ምስሉ ላይ ትልቅ የቀይ “FAKE” (ሐሰተኛ) የሚል ማህተም በማስቀመጥ ደጋፊዎቹ እና የሕዝብ አባላት በተሳሳተ መረጃ እንዳይደናገሩ አሳስቧል። እንደ ማህበሩ ገለጻ ከሆነ ይህ የተቀናበረ ሐሰተኛ መግለጫ የመነጨውና መጀመሪያ የተሰራጨው ከመንግስት ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ወይም "የገዥው አካል አፈቀላጤዎች ገጽ ላይ ነው" ብሏል። በተጨማሪም በአሜሪካ የአማራ ማህበር ማንኛውም አይነት ይፋዊ መግለጫ፣ መረጃና አቋም የሚለቀቀው በድርጅቱ ህጋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ብቻ መሆኑን አብራርቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የነበረውና የማህበሩ አርማ ያለበት መግለጫ ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ መሆኑን ድርጅቱ በመግለፁ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና መረጃዎችን ከተቋማቱ ህጋዊ ገጾች ብቻ እንዲከታተሉ ይመከራል። ኢትዮጵያ ቼክ!
613
#FactCheck በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ ጦር መሳሪያዎች በሚል በሰበር መልኩ እየተጋሩ ያሉ ምስሎች በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ናቸው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ‘በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ’ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። በምስሎቹ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ከሌሎች ሁለት ግለሰቦች ጋር ቆመው ከፊታቸው ደግሞ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያዎች ተደርድረው ይታያሉ። ምስሎቹን “ሰበር መረጃ” በማለት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። ይህ ገጽ “ከጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ ዛሬ ብቻ 75 ክላሽ 1ዲሽቃ 2 ብሬን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተረክቧል” የሚል ጽሁፍም ከምስሎቹ ጋር አጋርቷል። በተመሳሳይ መልኩ 'ሀገሬ ሚዲያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽም ምስሎቹን እና የጽሁፍ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 35 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገጹ የተጋራዉን መረጃ መልሰው አጋርተዉታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነውና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለማጣራት በሚረዳው ‘SynthID Detector’ በመጠቀም ምስሎቹን መርምሯል። በዚሁ መሰረት ምስሎቹ ጉግል ኤአይ (Google AI) በመጠቀም የተፈበረኩ መሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ (reverse image search) ባደረግነው ማጣራት አንዳንዶቹ ምስሎች ትክክለኛ የሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ምስልን ይዘት በመቀየር የተሰሩ መሆናቸዉን አረጋግጠናል። ትክክለኛው የጀነራሉ ምስል በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ትክክለኛና የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ከሁለት ቀናት በፊት የተጋራ ሲሆን በአማራ ክልል የተደረገን ኦፕሬሽን በማስመልከት የተጋራም ነበር፡ facebook.com/share/p/1BuimH7… የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከምስሉ ጋር ባጋራው የጽሁፍ 'ምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጣናዎች ባደረገው ፀረ-ሽምቅ ስምሪት ፈረስ ቤት ፣ ዋሸራ ፣ ጫት ዋርካ ፣ ሐሙስ ገበያ ፣ ሰከላ እና ሌሎች ቀጣናዎች የነበረው ፅንፈኛ ተደምስሷል’ ብሏል። የሰው-ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
3
8
3
16
2,463
#Explainer ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን? የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል፣ በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል። ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል። ተጨማሪ ያንብቡ: ethiopiacheck.org/home/disin…
1
1,088
#FactCheck የገቢዎች ሚኒስቴር ዴኤታዋ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮች ባሏቸው ገጾች እና ግለሰቦች ዘንድ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል የሚል ጽሁፍ (Caption) የተለጠፈበት ምስል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ እየተሰራጨ ያለው ምስል የፎቶ ማቀናበሪያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የተቀነባበረ እና ሀሰተኛ መረጃን ለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰራ መሆኑን አረጋግጠናል። ትክክለኛው እና ያልተቆረጠው ምስል የተወሰደው የገቢዎች ሚኒስቴር ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ካጋራው መረጃ ላይ ነው። ዋናው መረጃ የሚያወራው የዩናይትድ ኪንግደም የግብር፣ የክፍያ እና የጉምሩክ ባለሥልጣን (HMRC) በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሲያካሂደው የነበረውን የታክስ ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ድጋፍ (Tax Transformation Program) ማጠናቀቁን በሚመለከት ነው (ሊንክ: facebook.com/share/p/1A2mhcT…) በዚህ መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን የተሰራጨው ሀሰተኛ ምስል ከዚሁ እውነተኛ የፎቶ ስብስብ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ ነው። ቅንብሩን የሰሩት አካላይ ይህንን ትክክለኛ ምስል በመውሰድ፣ የቴሌቪዥን ዜና እይታውን ትክክለኛ በማስመሰል እና ከስሩ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" የሚል የሀሰት የሆነ ጽሁፍ በማስገባት አሰራጭተውታል። ማህበረሰቡ ይህ ምስል የተጭበረበረ እና ከእውነተኛ መረጃ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ መሆኑን ተገንዝቦ እንዲህ አይነቱን ሀሰተኛ መረጃ ከማመን እና ከማጋራት እንዲቆጠብ ኢትዮጵያ ቼክ ይመክራል። ኢትዮጵያ ቼክ!
1
2
778
#FactCheck የአርሰናል ደጋፊዎች ‘የዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን’ የሚል መልዕክት የያዘ ባነር ይዘዉ የተነሱት ፎቶ በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በቅንብር የተሰራ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ቀናት አርሰናል የ2025/2026 ውድድር ዘመን የእንግሊዙ አርሰናል የእግር ኳስ ክለብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን በማስመልከት የተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂደዋል። በዝግጅቶቹም የክለቡ የቀድሞ ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬን ጨምሮ የAFTV ሚዲያ አባላት ከክለቡ ደጋፊዎች ጋር ተገናኝተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ በቤተመንግስት ሙዝየም ውስጥ የተነሳ ምስል የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሲሆን መነጋገሪያም ሆኗል። ይህ ምስል ኢማኑኤል ኢቦዬን፤ የAFTV ሚዲያ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች/ የቡድኑ ደጋፊዎች “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ባነር ጀርባ ቆመዉ ይታያል። ምስሉን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘Wollo Addis’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ የሚገኝ ሲሆን ገጹ ያጋራውን ምስል ከ50 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ አጋርተዉታል፣ ከ2 ሸህ በላይ አስተያቶችም ተሰጥተዉበታል። ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ምስል ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የተለያዩ መገልገያዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም በምስሉ ላይ ጥልቅ ምልከታ እና የማመሳከር ስራ ሰርቷል። በቅድሚያ የተነካኩና ይዘታቸው የተቀየረ ምስሎችን ለመመርመር የሚረዳዉን ፎቶ ፎረንሲክስ ድረ-ገጽ በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት በምስሉ ዉስጥ የሚገኘውና “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር በቅንብር የተካተተ መሆኑን የሚያሳይ ትንተና አግኝተናል። በተጨማሪ ‘illuminarty.ai’ የተሰኘዉን ድረ-ገጽ በመጠቀም በባነሩ ላይ ባደረግነዉ ምርመራ ባነሩ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን (88%) የሚያሳይ መረጃ አግኝተናል። በሌላ በኩል ምስሉን በማግዘፍ ባደረግነው ጥልቅ ምርመራ ባነሩን ይዘው የሚታዩ እጆች ቅርጻቸው የተዛባ እና ትክክለኛ ያልሆኑ መሆናቸውን ተመልክተናል። በተጨማሪም በምስሉ በስተቀኝ ዳር ላይ የቆመ ግለሰብ የእጅ ጌጥ ምስሉ በመነካካቱ ይዘቱ የተቀየረ መሆኑን ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ በእለቱ የተነሱ እና የተቀረጹ ምስሎች እና ቪዲዮችን በመመልከትም የማመሳከር ስራ ሰርቷል። በቤተመንግስት ሙዝየም የተነሳውና ትክክለኛ ፎቶ ላይ በስተግራ ጥግ የሚገኝ ግለሰብ የታችኛው የእግር ክፍል ‘I love Addis Ababa’ በሚለው የፎቶ ፍሬም የተደበቀ ነው። ነገር ግን “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ላይ ግለሰቡ ጥቁር ቆዳ መሳይ ጫማ ተጫምቶ ይታያል። ኢትዮጵያ ቼክ የግለሰቡን የእለቱን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች የተመለከተ ሲሆን ግለሰቡ በእለቱ የተለያዩ ቀለማት ያለው ስኒከር ጫማ ተጫምቶ እንደነበር ተመልክቷል። ይህም ባነሩ ያለበት ምስል ከትክክለኛው ምስል ላይ ‘I love Addis Ababa’ ሚለውን የፎቶ ፍሬም በማጥፋት በምትኩ የግለሰቡ የታችኛው የእግር ክፍል ላይ በሰው-ሰራሽ ክህሎት ሀሰተኛ ጫማ የተካተተ መሆኑን አረጋግጠናል። በዚሁ መሰረት ከላይ የተዘረሩትን ቴክኖሎጂን እና የባለሙያ ምልከታን በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ትክክለኛ ያለሆነ እና በቅንብር የተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። ትክክለኛ ምስሎች ላይ የተፈበረኩ ይዘቶችን በመጨመር የሚጋሩ መልዕክቶች ለሀሰተኛ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
2
2
40
4,720
#FactCheck በረቀቀ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተጋራ የሚገኘው ቪዲዮ ምንነት /ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የፋኖ አባል ለመንግስት እጅ እንደሰጠ የሚጠቁም የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። ይህ የተሰራጨው የጽሁፍ መረጃ “የዘመነ ካሴ አብሮ አደግ እና የዘመነ ካሴ ቀኝ እጅ ቴዎድሮስ የደሜ የሚመራውን ታጣቂ አሰልፎ ወደ ሰላም መጥቷል” የሚል መልዕክት ያዘለ ነው። በተጨማሪም በቪዲዮው ላይ የሚታየዉ ግለሰብ “እኔና ጓደኞቼ ከመንግስት ጋር በመስማማት እጃችንን የሰጠን ሲሆን ከሻብያ ተላላኪዉ ዘመነ ካሴ ጋር የነበረን ግንኙነት በዚ አብቅቷል” ሲል በግልጽ ይደመጣል። ይህን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በስፋት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘የፍቅር መንገድ’ እና ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚባሉ የፌስቡክ ገጾች በዋነኝነት ይገኙበታል። በተለይም ‘የፍቅር መንገድ’ በተሰኘዉ ገጽ የተጋራዉን ይኸንን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ ከመቶ አርባ በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ለሌሎች ያጋሩት ሲሆን በርካታ አስተያየቶችም ተሰጥተዉበታል። ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ቪዲዮው ፈጽሞ እውነተኛ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነዉን ‘ሲንዝ አይዲ ዲቴክተር’ (SynthID Detector) የተባለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በመጠቀም በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተሰራጨው ምስል ትክክለኛ ሰውን እንደማያሳይ ደርሶበታል። በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት በቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ምስልም ሆነ የሚሰማው ድምጽ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተቀነባበረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። በቪዲዮው ላይ የሚታየው የከንፈር እንቅስቃሴ፣ የፊት ገጽታ እና የድምጽ ቅንብር አንድን ትክክለኛ ሰው አስመስሎ በኮምፒውተር ፕሮግራም የተሰራ እንጂ በገሃዱ ዓለም የተፈጠረን ክስተት የሚያንጸባርቅ አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ መሰል የዲፕፌክ (Deepfake) ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም እየተበራከቱ እና በርካታ ሰዎችን ለተሳሳተ መረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ። አጥፊ እና አሳሳች መረጃ አሰራጪ አካላት እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም እውነተኛ የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ። ይህ አይነቱ ቴክኖሎጂ የፖለቲካ ውዥንብር ለመፍጠር፣ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማራመድ፣ እና የሰዎችን ስነልቦና ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚሰራጭ አደገኛ የሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) መሳሪያ ሆኗል። በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ በማቅረብ ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃን አምኖ እንዲቀበል ማድረግ የተለመደ የማጭበርበር ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል። ሰዎች እውነተኛ ቪዲዮ እየተመለከቱ እንደሆነ በማሰብ እንዲታለሉ እና የተዛባ መረጃን ለሌሎች በማጋራት በማህበረሰቡ ውስጥ አለመተማመንን መፍጠር የዚህ አይነቱ ተግባር ዋና አላማ ነው። ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን እያደገ የመጣውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አደጋ በሚገባ ተገንዝበው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን። ማንኛውም አጠራጣሪ እና ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች ወይም ግለሰቦች የሚጋሩ የምስል እና የቪዲዮ መረጃዎችን ልክ እንዳዩት ከማመናችን እና መልሰን ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት ማድረግ አለብን። ቪዲዮዎች ያልተለመደ የዓይን ብልጭታ፣ ከድምጽ ጋር የማይሄድ የከንፈር እንቅስቃሴ ወይም ኢተፈጥሮአዊ የሆነ የቆዳ ገጽታ ካላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ቼክ!
3
6
1
16
2,817