Eyob Messafint (@eyobmes) header
Eyob Messafint (@eyobmes) profile picture
Addis Ababa
Joined August 2012
Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)Photo by Eyob Messafint (@eyobmes)
መስረም 30/2019 ዓ.ም. በክቡር የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዓብይ አሕመድ (ዶ/ር) በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴታነት ለተሰጠኝ ኃላፊነት ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ። የተሰጠኝን ኃላፊነት ለሀገራችንና ለህዝባችን ጥቅም ለማዋል ሕግን እና ርትዕን መሠረት አድርጌ ባለኝ አቅም ሁሉ እንደምተጋ ቃል እገባለሁ። ይኽን ኃላፊነት እንደምወጣ ተማምናችሁ በግሌም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ የመልካም ምኞታችሁን ለገለፃችሁልኝ ወዳጆቼ ሁሉ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ። #ኢዜማ
51
13
7
169
12,107
መስከረም 25/2019 ዓ.ም. በተመሠረተው መንግሥት በዛሬው ዕለት በሚኒስትሮች ም/ቤት ሚኒስቴርነት ለተሾማችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። መጪው የሥራ ዘመንም በወሰዳችሁት ኃላፊነት የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ እና በእያንዳንዱን ዜጋ ሕይወት ላይ በየዘርፉ በጎ አስተዋፅኦ የምታደርጉበት እንዲሆን እመኛለሁ። እንደ አንድ የናንተ ስኬት የሀገር ስኬት ነው ብሎ እንደሚያምን ዜጋ፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል እና የተፎካካሪ ፓርቲ መሪ በምንጋራቸው ርዕዮች ላይ እና ብሔራዊ ጥቅማችንን መሠረት ያደረገ ገንቢ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኔን እገልፃለሁ። በድጋሜ መልካም የሥራ ዘመን! © 📷 #PMOEthiopia
1
8
271
የመልካም ምኞት መግለጫ!! #ኢዜማ #ኢትዮጵያ
14
17
1
75
6,885
Baga Ayyaana Irreecha Bara 2019 Geessan! እንኳን ለ 2019 ዓ.ም. የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! #ኢዜማ #ኢትዮጵያ #ኢሬቻ #Irreechaa
1
2
13
1,043
የኢትዮጵያ እውነተኛ ታላቅነት መለኪያ ያለው የጋራ ቤታችን የምንላትን አገር በአንድነት ለመገንባት በምናሳየው ቆራጥነት ውስጥ ነው። ልዩነቶቻችንን አንዘነጋም፤ ዛሬ የገጠሙንን እውነተኛ ችግሮችም አቅልለን አንመለከትም። ነገር ግን አቅማችንን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ጠንካራና ዘላቂ ተቋማትን የመገንባት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ እንዲሁም ያልተነካውን ሰፊ ሐብታችንን ለትውልድ ወደሚሻገር ሐብት የመቀየር አቅም አለን። የኢትዮጵያ ተስፋ ለአንድ ወገን ብቻ የሚተው ወይም በጥቂቶች የሚሳካ አይደለም። መጪው ዘመናችን ለፍትህ ባለን የጋራ ኃላፊነት እና ለሰላም ባለን ቁርጠኝነት የሚቃኝ የጋራ ማንነታችን መገለጫ ሊሆን ይገባል። The true measure of Ethiopia’s greatness lies in our courage to unite and build the home we all share. We do not turn a blind eye to our differences, nor do we dismiss the genuine hardships of today. But we know what we are capable of, we have the power to build enduring institutions, uphold the rule of law, and transform our vast, untapped resources into generational wealth. Ethiopia’s promise is too great to be claimed by any single group. Our future belongs to every one of us, bound by a shared responsibility to justice and an unwavering commitment to peace. #ኢዜማ #EZEMA
7
2
1
18
2,907
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ
1
2
4
182
ባለፉት ጥቂት ቀናት በክልል ምክር ቤቶች እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጡንን ኃላፊነቶች ለመረከብ በምናደርገው ዝግጅት፣ ከተለያዩ አካባቢዎች በማኅበረሰቡ የውክልና ድምፅ ካገኙ የፓርቲያችን ተወካዮች ጋር ቆይታ አድርገናል። በውይይታችን ማዕከላዊ ትኩረት የነበረውም የኢዜማ የፖለቲካ ፍልስፍና የሆነው «ማኅበራዊ ፍትሕን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማረጋገጥ» የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ውይይታችን ከፖለቲካው ጫጫታ ባሻገር ያለውን አንድ መሠረታዊ እውነት ዳግም ያረጋገጠልን ነበር፤ ፍትሕ መፈክር ወይም የመከፋፈያ መሣሪያ ሳይሆን ለእኩል ዜግነት፣ ለገለልተኛ ተቋማት ግንባታ እና ለሁሉም ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ክብር በየዕለቱ የሚደረግ ተግባር መሆኑን ነው። እውነተኛ ለውጥ በመርሕ በሚመራ የፖለቲካ አመራር፣ በፍትሐዊነት፣ እንዲሁም ለማኅበረሰባችን በሚሰጥ የማይወላወልና እኩልነትን ባረጋገጠ አገልግሎት ደረጃ በደረጃ የሚገነባ ነው። Over the past few days, I spent time with elected EZEMA representatives from across our nation as we prepare to assume our respective roles in regional councils and the House of Peoples' Representatives (HoPR). A central focus of our discussions was EZEMA’s fundamental pillar: delivering genuine social justice to every Ethiopian. Our conversations reaffirmed a vital truth, beyond the political noise, justice is neither a slogan nor a weapon of division. Rather, it is a quiet, daily commitment to equal citizenship, impartial institutions, and economic dignity for all. Real change is never forged in divisiveness. It is built step-by-step through principled political leadership, fairness, and an unwavering, equitable service to our communities. #ኢዜማ #EZEMA
3
13
802
We were delighted to host Political Counsellor of British Embassy in Ethiopia, Rick Shear and his team at the EZEMA office today. We engaged in a highly productive discussion on current political affairs and explored how we can work together to cultivate a healthy political ecosystem. To cap it off, the team also took a short tour of our academy. የእንግሊዝ ኤምባሲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑትን ሪክ ሺር እና ቡድናቸውን በቢሯችን አግኝተን ስለ ኢትዮጵያ አሁናዊ የፖለቲካ ጉዳይ እና በቀጣይ በምን መልኩ በጋራ ልንሰራ እንደምንችል ተወያይተናል። እግረ መንገዳቸውንም የፓርቲያችንን የፖለቲካ አካዳሚ ጎብኝተዋል። @UKinEthiopia #EZEMA #ኢዜማ
7
328
መልካም አዲስ ዓመት!!
የኢዜማ መሪ ኢዮብ መሳፍንት የአዲስ ዓመት መልዕክት #ኢዜማ #ezema #ኢትዮጵያ #Ethiopia #አዲስ_ዓመት
2
10
866
Happy Africa Union Day! As we observe #AUDay2026 under the banner of “Assuring Sustainable Water Availability and Safe Sanitation Systems,” the goals of Agenda 2063 resonate deeply with our national purpose. Decades ago, Ethiopia stood at the forefront of the African Union's formation, championing continental unity and political liberation. Today, our historic responsibility must evolve to drive the continent's next great frontier, resource sovereignty and economic integration. The AU’s focus on water aligns perfectly with EZEMA’s core economic vision. We have consistently championed the equitable, rational, and sovereign utilization of our natural wealth. Water is not just a basic need; it is the absolute foundation of our economic dignity, food sovereignty, and energy independence. To honor our legacy as a unifying force in Africa, we must embrace a collaborative vision for our transboundary waters focusing on the prosperous future we can build together with our fellow Africans. True water security demands forward-thinking governance, relying on science based management, empowering our youth and technical experts, and leveraging modern infrastructure to drive shared regional prosperity. When Ethiopia harnesses its water resources responsibly and innovatively, we continue our historic pan-African leadership, turning shared potential into lasting peace. Let us build a self-reliant, climate-resilient continent. #EZEMA #ኢዜማ
2
9
299
የአዲስ ዓመት ንጋት እየቀረበ ሲመጣ፣ ያለፍንበትን ጉዞ ቆም ብለን እንድናስብበት እና ወደፊት የምንጓዝበትን መንገድ በተገቢ ሁኔታ እንድንቀርጽ ጊዜ ዕድል ይሰጠናል። እውነተኛ እድገት የግልና የሙያ ምኞቶቻችንን ከአገራችን እምቅ አቅምና ግልጽ ግንዛቤ ጋር እንድናያይዝ ይጠይቀናል። የምንመኛትን ኢትዮጵያ መገንባት ከእያንዳንዱ ዜጋ የማይናወጥ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። የመንግሥት ተቋማት ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ማጠናከር፣ ለሁሉም ዜጎች በብቃት፣ በታማኝነትና በፍትሕ እንዲያገለግሉ ማድረግ አለብን። በመንግሥት አገልግሎትም ሆነ በግሉ ዘርፍ፣ የየዕለቱ ተግባራችን የማኅበረሰባችንን የዜግነት እሴቶች፣ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችና የጋራ ባህል በቀጥታ ይቀርጻል። በዚህ ሁሉ እያንዳንዱ ዘመን የራሱን ተልዕኮ ይጠይቃል። የዛሬው ታላቅ ኃላፊነታችን ደግሞ በመርህ ላይ የተመሠረተ ትብብርን መገንባት እና የጋራ ጥረታችንን ወደ ዘላቂ ሰላም፣ ወደ ተቋማዊ ክብር እና ወደ ዘላቂ አገራዊ ሁሉን አቀፍ ዕድገት ማዞር ነው። As the dawn of a new year approaches, we are called to pause and reflect on the journey behind us while deliberately shaping the path ahead. True progress demands that we ground our personal and professional aspirations in a clear recognition of our national potential. Constructing the Ethiopia we envision requires an unyielding commitment from every citizen, we must fortify our state institutions to their full capacity, ensuring they serve all people with competence, integrity, and justice. Whether in public service or the private sector, our daily actions directly cultivate the civic norms, democratic values, and shared culture that define us. Every era demands its own purpose. Today, our paramount duty is to forge principled collaboration turning our collective efforts toward enduring peace, institutional dignity, and sustainable national growth. #ኢዜማ #EZEMA
1
3
9
299
Congratulations Africa! The UN’s decision to correct the world map and give our continent its true, proportional size is a crucial symbolic milestone. For centuries, 16th-century projections shrank a vast continent in reality 14 times larger than Greenland into a footnote, distorting our place in the global consciousness. Size matters, but map distortion is only a symptom. The deeper misrepresentation spans every front of importance:- The Economic Reality, Depicting Africa as dependent on the West, when the reverse is true. A rich continent endowed with immense natural resources is reduced to a lens of aid and poverty. The Human Reality, Framing a resilient population of 1.5 billion people as mere recipients rather than drivers of the world’s future even as our demographic weight reaches one-fifth of humanity. The Global Contradiction, The world historically relies on Africa’s land, labor, minerals, energy, and markets to power global industries, yet Africa captures only a fraction of the value created. Symbolism is where true change begins. A map isn't just paper; it dictates what generations view as large or small, central or peripheral. The map has been corrected. Now, Africa must correct the much bigger map: the map of global power, opportunity, and influence. We must demand equal treatment, fair economic relationships, true ownership of our resources, and an end to speaking about Africa without Africa at the table. We must use this momentum to claim our rightful place. IT’S TIME FOR AFRICA. #EZEMA #ኢዜማ
4
16
331
የቤቶች አቅርቦትና የኢዜማ የምርጫ ማኒፌስቶ ኢዜማ ለ2018 ምርጫ ባዘጋጀው ማኒፌስቶ ላይ የቤቶች ግንባታን በሚመለከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ባንኮች በሚያዋጡትና በባለቤትነት በሚይዙት መንገድ የሚቋቋም ሙሉ አላማው የቤቶች ባንክ (Mortgage bank) የሆነ ተቋም እንዲገነባ አዲስ ሀሳብ ይዞ ብቅ ብሎ ነበር። ይህ ባንክ በትልቅ ካፒታል የሚቋቋም በመሆኑ እንዲሁም ብቃቱና ልምዱ ባላቸው ባንኮች ሚተገበር በመሆኑ ለሀገራችን በተለይም እንደ አዲስ አበባ ላሉ ከፍተኛ የቤት ፍላጎት ላለባቸውና በአቅርቦት ማስታገስ ባልተቻለባቸው ከተሞች ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ይኖረዋል። ለሀገራችን ችግር ሀገራዊ መፍትሄ መሆኑም አያጠራጥርም። በሀገራችን ያሉ የተለያዩ ችግሮቻችን በተለይም የምርት እጥረቶች መፈታት ያለባቸው በዚህ አይነት ሀገር በቀል የመፍትሄ አማራጮች መሆን አለበት ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ዛሬ በሰማሁት ዜና ደግሞ መንግስት ይህንን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት “የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለል ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል መፈረሙን” ሰምተናል። የትብብር ማዕቀፉ በ100 ቢልየን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የሚቋቋም በመሆኑ ለቤቶች ግንባታ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አቅርቦት ለማስጀመር የሚያስችል መሆኑ እሙን ነው። ነገር ግን የቤቶች አቅርቦት ችግር የካፒታል እጥረት ብቻ ባለመሆኑ ራሱን የቻለ የአሰራር ማዕቀፍ ያስፈልገዋል። ብሔራዊ ባንክ ተቆጣጣሪ ተቋም እንጂ በራሱ ፈፃሚ ተቋም ባለመሆኑ ፈፃሚው ማነው? ገንዘቡ ወደ ገበያው የሚገባው በምን መንገድ ነው? ምዝበራን ለማስቀረት ምን አይነት የቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል? ከዚህ በፊት በመንግስት የሚገነቡ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን ብክነት እና የጥራት ችግር በምን መንገድ መፍታት ይቻላል? የሚሉት ቁልፍ ጥያቄዎች ከአሁኑ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል። የዚህ አይነት ትልሞች ሊበረታቱ የሚገቡና በቀጣይም በሌሎች ዘርፎች ሊታሰብባቸው የሚገባ ናቸው። ሀሳብን ወደ መሬት ማውረድ ላይ እንደ ሀገር ያሉብንን ውስንነቶች እና ሁሉን ነገር በዘመቻ መልክ መስራትን በማረም ተግባራዊ እንደሚደረጉ እንዲሁም ከላይ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ቀድመው መልስ እንደሚያገኙ እምነቴ ነው። #EZEMA #ኢዜማ
12
5
41
3,465
እውነተኛ አገራዊ ዕድገት በሁለት የማይነጣጠሉ ምሰሶዎች ላይ ይቆማል፤ ጠንካራ ሀገራዊ (ማክሮ) ኢኮኖሚ መገንባት እና የእያንዳንዱን ዜጋ (ማይክሮ) የኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ። በሀገራችን እየተካሄዱ ያሉት መዋቅራዊ ማሻሻያዎችና የኢኮኖሚ ዘመናዊነት ጠንካራ አገራዊ መሠረት እየጣሉ ቢሆንም፣ የእውነተኛ ስኬት መለኪያው ግን እነዚህ ለውጦች በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ምን ያህል ተጨባጭ መሻሻል እንዳመጡ በመለካት የሚመዘን ነው። የኢዜማ የኢኮኖሚ ራዕይ ዋና ማጠንጠኛም እነዚህን ሁለት የዕድገት ምሰሶዎች በማስተሳሰር፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት በዜጎች ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ ነው። ሀገራዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ወደ ተጨባጭ የኑሮ እፎይታ የሚቀይሩ፣ አነስተኛና የአካባቢ ንግዶችን የሚያጠናክሩ፣ የዋጋ ንረትን የሚገቱ እና በብዙ ድካም የተገኘው የሀገራችን የዕድገት ፍሬ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ማዕድ ላይ እንዲደርስ የሚያረጋግጡ የተጠኑና የታለሙ ፖሊሲዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ኢዜማ በጽኑ ይቆማል። True national development relies on two inseparable pillars, macro-level strength and micro-level empowerment. The structural reforms and economic modernization unfolding across our country set a strong national stage, but the true test of success is how effectively those gains translate into the daily life of the average citizen. EZEMA’s economic vision centers on completing this equation. We advocate for targeted policies that channel national momentum into tangible relief, strengthening neighborhood businesses, curbing inflation, and ensuring that the rewards of our country's hard-won progress are felt at the dining table of every Ethiopian family. #EZEMA #ኢዜማ
5
3
12
628
As we end the week and prepare to navigate a start to another week, it is worth to take note of the broader path we are undertaking as a nation. Ethiopia is currently making vital strides toward economic growth, digital transformation, and much-needed structural reforms, but we must always remember that genuine nation-building, much like democracy itself, is a continuous journey of endurance, not an overnight achievement. Our ongoing efforts to foster nationwide consensus offer us a critical opportunity to thoughtfully amend past fractures and strengthen our shared institutional foundations. The undeniable energy and resilience of our youth continuously remind us that the appetite for a better, more united Ethiopia is stronger than ever. Let us stay the course. True progress will be realized when our economic and technological advancements are firmly anchored in social justice, active civic participation, and an unshakeable commitment to the dignity of every Ethiopian. Let’s keep moving forward with steady, purposeful resolve. #EZEMA #ኢዜማ
1
6
412
👉 በዛሬው የፓርቲያችን መግለጫ ላይ የተቀመጡ ማሳሰቢያዎች የምክክር ሒደቱ የመመካከሪያ ምዕራፉ ቢጠናቀቅም የሒደቱ ወሳኝ ምዕራፍ የሆኑት በኮሚሽኑ የመጨረሻውን ምክረ ሀሳቦች ለመንግሥትና ለህዝብ የሚያቀርቡበት ሂደት እና የትግበራ ሂደት ገና ይቀራል። እነዚህ ሁለት ዋና ምዕራፎችም በጥንቃቄ እንዲያዙ ኢዜማ የሚከተሉትን አምስት ማሳሰቢያዎች መስጠት ይወዳል፡፡ 1. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመንግሥትና ለሕዝብ የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦችን በሚያቀርብበት ወቅት በአጠቃላይ የምክክሩን መንፈስ እና የተመካካሪዎችን በንባብ የቀረበውን የመጨረሻ ምክረ-ሀሳብ ብቻ ባከበረ መልኩ እንዲሆን፤ 2. ኮሚሽኑ በተመካካሪዎች የቀረቡትን 400 ምክረ ሀሳቦች ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ፤ 3. በምክክሩ ሒደት ከጥቃቅን ቡድኖች ጀምሮ ያደረግናቸውን ውይይቶች ቃለጉባዔዎች በማገናዘብ እንዲከወን፤ እንዲሁም በማቋቋሚያ አዋጁ መሰረት የምክረ ሀሳቦቹን አፈፃፀም እንዲከታተል፤ 4. መንግሥት የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውጤታማ የሚሆነው የቀረቡት ምክረ ሀሳቦች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረጉ እንደመሆኑ አፈፃፀሙም ከተገቢው በላይ ግዜ እንዳይወስድ በፍጥነት እንዲፈፀም እንዲያደርግ ፤ 5. የሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል ገለልተኛ እና ሕጋዊ አካል አንዲቋቋም እንጠይቃለን። በመጨረሻም ሀገራዊ ምክክሮችን በማድረግ ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የምናደርገው ሒደት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን፤ በዚህ ረጅም ሀገራዊ ምክክር ውስጥ የተስተዋሉ የሒደት ጉድለቶች ቢኖሩም እንኳን በመጨረሻ የመጣው ውጤት የሚያበረታታ፤ ተስፋ ሰጪ እና የመመካከርን አስፈላጊነት በጉልህ ያሳየ፣ እንደ ሀገርም በጣም ጠቃሚ ፣ እንደ ፓርቲም ብዙ የተማርንበት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
13
6
7
33
7,789
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ መልካም የመውሊድ በዓል እመኛለሁ። Wishing a happy Mawlid to all my Muslim brothers and sisters. #ኢዜማ #EZEMA
2
14
448
I bid farewell to my dear brother and a true friend of Ethiopia, H.E. Ambassador Stian Christensen @NorwayinAddis, as he concludes his four year tenure as Norway’s Ambassador to Ethiopia.Throughout his time here, Amb Christensen has done remarkable work, not only in strengthening the bilateral ties between our two nations, but also in fostering deep, meaningful citizen diplomacy that brings our peoples closer together. I am truly glad I had the opportunity to personally thank him for his outstanding service over a cup of Ethiopian coffee. On behalf of myself and EZEMA, I look forward to our continued engagement and wish you every success and fulfillment in your next assignment. You leave with our appreciation, but certainly not as a stranger. You will always have a friend in Ethiopia. #EZEMA
4
1
17
2,417
የእሁድ ማለዳ ከዕለት ተዕለት ጫና ትንሽ ፋታ ወስደን፣ የወቅቱን ከባድነትና የተሸከምነውን ኃላፊነት የምናስብበት ጊዜ ይሰጠናል። በተለይም ፍትሐዊት፣ አንድነቷ የተጠበቀና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚናፍቁ ሚሊዮኖችን ተስፋና ምኞት ይዘን እንደ ኢዜማ በሀገራዊ ምክክሩ መድረክ ላይ እየተሳተፍን ባለንበት በዚህ ወቅት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል። አንድ ነገር በግልጽ ላስቀምጥ፤ ኢዜማ ወደዚህ ምክክር የገባው በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ለመሳተፍ ወይም በአጭር ጊዜ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ለመደራደር አይደለም። የመጣነው መሠረታዊና ሥርዓታዊ ለውጥ እንዲመጣ ለመታገል ነው። ኢዜማ እስከ ምክክሩ የመጨረሻ ቀን ድረስ፣ በማይበገር አቋም የሚከተሉትን ሶስት መሠረታዊ ምሠሦዎች ያራምዳል፦ 1. የማንደራደርበት የዜግነት ፖለቲካ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሙሉ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችን ቀዳሚና የማይደፈር መሠረት መሆን አለበት። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለው መብት፣ ክብርና ዕድል በማንነቱ ወይም በሚኖርበት አካባቢ ሊወሰን፣ ሊገደብ ወይም ሊነፈግ ፈጽሞ አይገባም። 2. እውነተኛ ነፃና ገለልተኛ የመንግሥት ተቋማት የፍትሕ አካላት፣ የሲቪል ሰርቪስ፣ የምርጫ ተቋማትና የፀጥታ ኃይሎች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነትና ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆን አለባቸው። መንግሥታት ይመጣሉ፤ ይሄዳሉ። ተቋማት ግን የሕገ መንግሥቱና የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ መሆን አለባቸው። 3. በዘመድ አዝማድና በፖለቲካዊ ወገንተኝነት ሳይሆን በብቃት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ሙስናን እንዲሁም በመንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ ገበያን ጠቅልለው የያዙ አካላትንና የጥቅም ትስስርን ማፍረስ ይገባል። ወጣት ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች በግንኙነት ወይም በወገንተኝነት ሳይሆን፣ በብቃታቸው፣ በፈጠራ ችሎታቸውና በትጋታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን ሥርዓት መገንባት አለብን። አንድ ሀገር በትናንት ግጭቶቿ ታስራ ወደፊት መፈተን አትችልም። ለኢትዮጵያ ወጣቶች፤ በዚህ የምክክር ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጥነው የመከፋፈልንና የግጭትን አዙሪት ለመስበር፣ ለወደፊት ሕይወታችሁም የሚመጥን ጠንካራ ሀገራዊ ሥርዓት ለመገንባት ነው። ኢዜማ እነዚህ መርሆች የሪፐብሊካችን የዕለት ተዕለት እውነታ እስኪሆኑ ድረስ በጽናት ይቆማል፤ ያለማቋረጥም ይታገልላቸዋል። የጋራ ዕጣ ፈንታችን ከተከፋፈለው ታሪካችን እጅግ የላቀ ነው። የዜጋ ክብር ፍጹምና የማይደፈር የሆነባትን ኢትዮጵያ በጋራ እንገንባ። የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ሰላማዊና የማሰላሰል ጊዜ የሞላበት መልካም የእረፍት ጊዜ እንደነበር በመተማመን መጪው ሳምንት ብሩህ እንዲሆንልን እመኛለሁ። #ኢዜማ #EZEMA
22
6
1
25
2,826