ዜና እረፍት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው አልፏል።
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ። ይበቊዐኒ ዘብየ እመአፈ ጻድቃን ቅዳሴ። ጽጌ መድኀኒት ማርያም ዘሠረጽኪ እም ሥርወ እሴ። እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ ተአምረኪ የአኵት ብናሴ
ድንግል ሆይ " ከኃጢአተኛ አፍ ምስጋና ለምኔ ፤ ከጻድቃን አፍ የሚቀርብልኝ ምስጋና ይበቃኛል " አትበዪ ፤ ከዕሤይ ሥር የበቀልሽ የመድኀኒት አበባ ማርያም ሆይ ፤ እኔን በደለኛውን ብትቀበዪ ተአምርሽን ጨረቃ ያመሰግናል።
ማሕሌተ ዘጽጌ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሳልሳይ እና በብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ሥርዓተ ቀብር ላይ ተገኝተው ለተሰበሰበ ሕዝብ አጽናንተዋል።
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ(ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊ፣ የድሬዳዋና የጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ፫ ኛ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር ) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በረከታቸው ይደርብን።
ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ መጋቢት ፩/፳፻፲፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የቅድስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በላከው መረጃ ገልጿል። ሥርዓተ ቀብራቸው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ተከብሯል።
ፎቶ አምሀ ያረጋል





















